ነገሮችን ከመሰረታቸው ለመለዳት አጀማመራቸውን እና የሄዱበትን መንገድ ማወቅ አስፈላጊ ይመስለኛል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከአንድ የፊልም ባለሙያ ጓደኛዬ ጋር  እየተወያየን ኮምፒይተሮች ባልነበሩበት ግዜ ፊልም እንዴት ኤዲት እንደሚደረግ ጠይቆኝ ነበር።ለሱም ለእናንተም ያነበብኩትን ላካፍላችሁ።

የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ምስል, Moving picture, ማሳያ መሳሪያ የተፈጠረው በ1879ዓ.ም ኤድዋርድ ሙይብሪጅ በሚባል ሰው ነበር። የሰራውም ማሽን ዞፕራዚስኮፕ ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህ መሳሪያ ተከታታይ ምስሎችን በፍጥነት በሚሽከረከር የመስታወት ዲስክ ላይ በማረግ የእንቅስቃሴን ምስል መፍጠር ችሎ ነበር። ነገር ግን፤ በመላው አለም የተንቀሳቃሽ ምስል ገበያ ውስጥ ሰርጎ ሊገባ የቻለው ከዞፕራዚስኮፕ በኋላ የመጣው ካይንቲስኮፕ የተባለ በታዋቂው አሜሪካዊ ፈጣሪ ቶማስ ኤዲሰን እና በሰራተኛው ዊልያም ዲክሰን በ1894 ዓ.ም የተሰራው ነበር። ከዚህ ጊዜ በኋላ ይህ ማሽን በተለያዩ የአለም አገራት እየዞረ ታየ። ያገኘውም ትርፍ በዚያን ግዜ በጣም ትልቅ ነበር። ሰዎችንም በተንቀሳቃሽ ምስል ማዝናናት እንደሚቻል እና ትልቅ የስራ ዘርፍ መሆኑን በመረዳታቸው ብዙ ታላላቅ እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ። ይታዩ የነበሩት ፊልሞች ግን እንደ ቲያትር አንድ ወጥ ነበሩ።

በታህሳስ 28, 1985ዓ.ም እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሚታዩበት ወቅት ከተመልካቾቹ ውስጥ ጆርጅ ሚሌስ የተባለ በወቅቱ የነበረ የአስማት ባለሙያ ስራው እጅግ በጣም ስቦት ነበር። ከዛም ግዜ በኋላ ከ500 በላይ አጫጭር ፊልሞችን መስራት ችሎ ነበር። ስራዎቹም ለዘመናዊ ቪዡዋል ኢፌክት ፈር ቀዳጅ ነበሩ። የፊልም ኤዲቲንግንም የተለያዩ ቴክኒኮች፤ ፌድ ኢን እና ፌድ አውት፤ ዲዞልቭ፤ እንዲሁም Stop motion photography መሰረት ጥሎ ነበር። ይህ ባለሙያ ግን ሁሉም ፊልሞቹ ካሜራው ሳይንቀሳቀስ የተሰሩ ነበሩ።

ከ1908ዓ.ም በኋላዴቪድ ዋልት ግሪፍን የተባለ አሜሪካዊ የፊልም ባለሙያContinutiy Editing የሚል የፊልም ተግባራዊ ፍልስፍና/ሀሳብ ጀምሮ ነበር። ይህ ሀሳብ የሚያተኩረው በአንድ ስነምድራዊ አቀማመጥ እና ግዜ የሚደረጉ ትዕይንቶችን በአንድ ላይ ማጣመርን ነበር።

ሌቭ ኩሽሎቭየተባለ የሶቬት ዩኒየን /ራሺያ/ የፊልም ባለሙያ በተመሳሳይ ግዜ ባደረገው ጥናት የኩልሾቭ አፌክትተብሎ የተሰየመ ታላቅ መደምደሚያ ላይ ደርሶ ነበር።

የኩልሾቭ አፌክት:የምስል/ቀረፃ ትርጉም ወይም በተመልካቹ ውስጥ የሚፈጥረው ስሜት የሚወሰነው በምስሉ ውስጥ በሚታዩት ነገሮች ብቻ ሳይሆን በምስሉ አደራደር ጭምር ነው።

、1154654564646546464564655464645646464646picture here…….6+45646

በዚሁ ግዜ በሶቬት ዩኒየን /ራሺያ/ ሰርጌ አንስታይን የተባለ የሌቭ ኩሽሎቭ ተማሪ የነበረ የፊልም ባለሙያThe Soviet Montage ተብሎ የሚጠራ የፊልም ኤዲቲንግ ፍልስፍና ጀምሮ ነበር። በ-Soviet Montage አስተሳሰብ አንድ ቀረፃ/ምስል በሌላ ቀረፃ/ምስል ሲተካ/ሲቀጥል በተመልካቹ ውስጥ የሚፈጥረውን ስሜት በድጋሚም ከሌላ ቀረፃ/ምስል ጋር በማጣመር ፊልሙ ታሪኩን እንደጠበቀ ወደፊት ማሰኬድ ይቻላል።

በዘመኑ ለፊልም ኤዲቲንግ አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎች ከመቀስ እና ማጣበቂያ የዘለሉ አልነበሩም።ኤዲቲንግ ጥበብ ሳይሆን የጉልበት ስራ ነበር። በ1906ዓ.ም በደች ተመራማሪው አይዋን ሰሪውረርተሰርቶሞቪላተብሎ ይጠራ የነበረው የቤት ውስጥ ፊልም ማጫወቺያ በ1924ዓ.ም እንደ ኢዲቲንግ መሳሪያነት ድጋሚ ታድሶ ለገበያ ቀረበ። ትልቅ ስኬትም ተጎናፅፎ ነበር።

በ1930ዓ.ም በጀርመናዊው ተመራማሪ ዊልሀም ስቴንቤክ የተሰራው በስሙ ይጠራ የነበረው ስቴንቤክ ማሽን የፊልም ዘንጎቹን በጠፍጣፋ ወለል ላይ በመዘርጋት እንዲሁም የፊልሙን ዘንጎች ምስል በስክሪን ላይ በማሳየቱ በመጠኑ የተሻለ ሂደትን መፍጠር ችሎ ነበር።  ይህ  ቀጥተኛ ኤዲቲንግ/linear editing/ ሂደት ምስሎችን በተራ በተራ በመደርደር የሚካሄድ ነበር። የመጀመሪያውን ምስል ማስተካከል ከተፈለገ ከዛ ምስል በኋላ የተሰሩትን  ኤዲቶች መመለስ ግድ ነበር።

ቀጥተኛ ያልሆነ ኤዲቲንግ/non linear editing/ : በዚህ የኤዲቲንግ ሂደት ፊልምን ኮምፒውተር ላይ ስካን በማድረግ ልክ እንደ ፅሁፍ በማነኛውም የፊልሙ ሰአት አፍራሽ ባልሆነ መልኩ በፍጥነት እና በትክክል መቁረጥ፤ መቀጠል፤ ማርዘም፤ ማሳጠር እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን መሰራት ይቻላል።

በ1971ዓ.ም የመጀመሪያው ቀጥተኛ ያልሆነ ኤዲቲንግን /non linear editing/ ማከናወን የሚችልcmx 600 የተባለ ሜንፍሬም ኮምፒውተርን በመጠቀም የልብስ ማጠቢያ  በሚያክል ማሽን ላይ በትልቁ ግማሽ ሰዓት ብቻ የሚያክል ቀረፃ ኤዲት ማድረግ የሚችል ሂደትን መስራት ችሎ ነበር። ነገር ግን ይህ ማሽን እጅግ በጣም ውድ ነበር።

ተመጣጣኝ ዋጋ እና መጠን ያላቸውን ማሽኖች እና ሂደቶች የመመስረቱ ሂደት አቪድ_1 በ1989ዓ.ም እስከሚመጣ ድረስ ብዙም የተሳካ አልነበረም። ከዚህ ግዜ በኋላም እድገቱ እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ቀጥሎ በተልያዩ ኢንጅነሮች እና የኮምፒውተር ተመራማሪዎች ጥረት ምክንያት አሁን ያለንበት ግዜ ላይ ልንደርስ ችለናል። በአሁኑ ግዜም ብዙ ካምፓኒዎች የተለያዩ ኤዲት ማድረጊያ ሶፍትዌሮችን በመስራት ማንኛውም ሰው ሊጠቀምበት በሚችለው መልኩ ማሰራጨት ጀምረዋል።

በመጨረሻም አሁን ያለንበት ግዜ አልፎ ከ10 እና 20 ዓመታት በኋላ ወደፊት ሊመጡ የሚችሉት ሂደቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ እጅግ በጣም ከባድ እና አጓጊ ይመስለኛል። እንደኔ ሀሳብ ግን አንድ የፊልም ባለሙያታሪኩን በተመልካቹ ልቦና ላይ ሊያሳድር የሚችለው በሚጠቀምበት ሂደት ወይንም ሶፍትዌር ሳይሆን ባለሙያው ባለው የጥበብ ችሎታ እና መግለፅ በፈልገበት መንገድ ይመስለኛል። ጥያቄውን በጥቂትም ቢሆን ለእናንተም ለጓደኛዬም የመለስኩ ይመስለኛል።

እርሶስ ስለኤዲቲንግ ምን የሚሉት አለ?በሚቀጥለው ፅሁፍስ ስለምን ማወቅ ይፈልጋሉ?ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ይፃፉልኝ።

ሰማኝጌታ አይችሉህም፤ ኪያ