አብዛኛውን ግዜ ማነኛውንም ነገር ለማወቅ ፈልጌ ኢንተርኔት ላይ ሰርች በማደርግበት ግዜ የማያቸው ርዕሶች እንደዚህ ፅሁፍ ርዕስ ናቸው፤  10 በአጭሩ ሰኬታማ የሚሆኑባቸው መንገዶች, 10 ሊመገቧቸው የሚገቡ ጤናማ ምግቦች, 10 የፍቅር ጓደኛዎን የሚያስደስቱባቸው መንገዶች፤ በአጠቃላይ ኢንተርኔት ላይ ለሁሉም ነገር 10 መንገዶች አሉ።አሁን ደግም እኔ ያነበብኩትን 10 ሊያውቋቸው የሚገቡ መሰረታዊ የዲጂታል ሲኒማቶግራፊ ሀሳቦች ላካፍላችሁ።

  1. Frame Rate: ቪዲዮ ወይም ፊልም የምንለው የምስሎች ቅንብር ነው። ምስሎች በየተራ በፍጥነት በሚታዩበት ግዜ ቪዲዮ ወይም ፊልም ይስጡናል፤በአንድ ሰከንድ የሚታዩትንየምስሎች ቁጥር Frame rate ብለን እንጠራዋለን። የተለያዩ ፍሬም ሬቶች የተለያዩ የምስል እንቅስቃሴን ይሰጡናል። የፊልሞች standard/ቋሚ frame rate 24 ፍሬሞች በሰከንድ (fps) ነው። ትልልቅ ፍሬም ሬቶችን መጠቀም ቀረፃውን ወደ 24fps በመቀየር ንፁህ እና ጥራት ያለው slow motion እንድናገኝ ይረዳናል።

 

  1. Progressive እና Interlace Scanning

Interlace scanning: በ1930ዎቹ ለCRT(cathode ray tube) ሞኒተሮች የተሰራ የምስል ማስተላለፊያ ዘዴ ነው።  የበፊት የቴሌቭዥን ሲስተሞች አንድ ሙሉ ፍሬምን በአንድ ግዜ ለማስተላለፍ ቀርፋፋ እና ደካማ ነበሩ። ይህም ሲሲተም ከፍሬሙ ላይኛው  ክፍል በመነሳት ጎዶሎ ቁጥር መስመሮችን (1,3,5….) እያስተላለፈ ይሄዳል፤ ይህም Upper field ወይም Odd field ይባላል። ከዛም ወደላይ በመመለስ የመጀመሪያውን መስመር በመዝለል ከሁለተኛው ጀምሮ (2,4,6…..) ያስተላልፋል፤ ይህም Lower field ወይም Even field ይባላል። እነዚህ ፊልዶች በፍጥነት ሲከታተሉ አንድ ሙሉ frame/ምስል ይሆናሉ ስለዚህም በ30ፍሬም/ሰከንድ interlace ምስል ውስጥ 60 ፊልዶች ይኖራሉ።

ከInterlace scanning ችግሮች መካከል የመስመሮች መዛባት ወይንም Aliasing የምንለው አንደኛው ከመሆኑም በላይ ፊልዶቹ በየተራ ስለሚተላለፉ ያነሰ ጥራት ይኖረዋል። Interlace scanning እየቀረ የመጣ የምስል ማስተላለፊያ ሲስተም ነው።

Progressive scanning: አንድ ካሜራ Progressive scanning በሚጠቀምበት ግዜ ፍሬሙ/ምስሉ በአንድ ግዜ ይቀረፃል/ይተላለፋል፤ ይህም ሂደት በጣም ንፁህ እና ጥራት ያለው ምስል ይሰጠናል። አብዛኞቹ ዲጂታል ካሜራዎች Progressive scanningን ይጠቀማሉ። በProgressive የተቀረፀን ከተፈለገ ወደ Interlace መቀየር ስለሚቻል ሁልግዜም በProgressive  መቅረፅ እንደዋነኛ አማራጭ አድርገን መውሰድ ይኖርብናል።

  1. Aspect ratio እና Anamorphic lenses

Aspect ratio: የአንድ ምስልን መጠን የምንገልፅበት ቃል ሲሆን የሚወክለውም የአንድ ምስል አግድም (width) ለቁመቱ (height) ያለውን ንፅፅር ነው። የwide screen ምስል 16:9 aspect ratio ሲኖረው የኢትዮጲያ ቲቪ ጣቢያ የሚጠቀመው ደግሞ standard definition 4:3 aspect ratio ነው። አብዛኞቹ በ2.35:1 aspect ratio የሚቀረፁ የሲኒማ ፊልሞች በAnamorphic cine lenses ነው።

Anamorphic lenses: ከተለመዱት ክብ (spherical) ሌንሶች የሚለዩት ሰፊ ምስልን አግድም በመጨፍለቅ የካሜራውን ሴንሰር በሚሞላ የምስል frame መለወጣቸው ነው። በዚህ ሌንስ የሚታዩ ምስሎች የተዛባ ሊመስሉ ይችላሉ፤ሰዎች ረዝመው ክቦች ደሞ ተለጥጠው ይታያሉ፤ ወደ ትክክለኛው ምስል የመቀየሩን ሂደት ምስሉን የሚያሳየው ፕሮጀክተር/ቪውፊይንደር ይወጣዋል።

  1. Shutter speed

ምስል የብርሀን ውጤት ነው። የካሜራው ሴንሰር ለምን ያህል ግዜ ለብርሀን እንደተጋለጠ የምንለካበት መንገድ shutter speed ይባላል። shutter speed የምስሉን የብርሀን መጠን እና በምስሉ ውስጥ ያለውን የእንቅስቃሴ ገለፃን ይወስናል።በዲጂታል ካሜራ ግዜ shutter speedንየፍሬም ሬቱን እጥፍ በማድረግ ይበልጥ ፊልማዊ ወይም አሳማኝ እንዲሁም የማይረብሽ የእንቅሰቃሴ ገለፃን ማግኘት እንችላለን፤ ማለትም ለ24fps ምስል 1/50, ለ30fps ምስል 1/60፤ ይሆናል። አንስተኛ shutter speed የፈካ እና እንቅስቃሴዎቹ ለስላሳና ደበዛዛየሆኑ ምስል ሲሰጠን ከፍተኛ shutter speed ደግሞ በተቃራኒው የጨለመ እና ጥራት ያለው የሚንገጫገጭ  ምስል ይሰጠናል።

 

  1. Focal length

ሌንስ የካሜራ አይን ነው። ወደ ሌንሱ የሚገባው ብርሃን ወደ አንድ ነጥብ የሚሰበሰብበት ቦታ Focal plane ይባላል።  የሌንሱን የማየት ብቃት የምንለካበት መንገድ ደግሞ Focal length ይባላል። በሌላ አገላለፅ Focal length ማለት ከሌንሱ እሰከ Focal plane ያለው ርቀት ነው።

Prime ሌንሶች አንድ ቋሚ የሆነ focal length ሲኖራቸው Zoom ሌንሶች ደግሞ የተለያዩ ስፋት ይኖራቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ረጅም Focal length ያላቸው ሌንሶች የጠበበ የእይታ መስኮት ወይም narrow angle of view ሲኖራቸው ያነሰ Focal length ያላቸው ደግሞ ሰፊ የእይታ መስኮት ወይም wide angle of view ይኖራቸዋል።

  1. Exposure and Aperture

Exposure: ማለት ወደ ዲጂታል ካሜራው እንዲገባ የተፈቀደው የብርሃን መጠን ነው። Exposureን ከምንቆጣጠርበት መንገዶች መካከል shutter speed እና Aperture ዋነኞቹ ናቸው።

Aperture: ወደ አንድ ሌንስ የሚገባውን የብርሃን መጠን በተቀያያሪ የብርሃን ማስገቢያ ክፍተት የምንቆጣጠርበት መንገድ ነው፤ የሚያልፈውን የብርሃን መጠን ደግሞ  በ F-stop ወይም በ T-stop እንገልፀዋለን፤  F-stop በሂሳብ ቀመር ተሰርቶ የሚገኝ ሲሆን T-stop ደግሞ ተለክቶ የሚገኝ ቁጥር ነው።

የAperture ክፍተት የሚቆጣጠረው የሚገባውን የብርሃን መጠን ብቻ ሳይሆን የሚገባው ብርሃን የካሜራውን ሴንሰር የሚመታበትን አንግልም ጭምር ነው። አንድ ሌንስ ጠባብ የaperture ክፍተት(ትልቅ የF-stop ቁጥር) ሲኖረው wide depth of field ወይም ሁሉም ነገር ጥርት ብሎ ይታያል፤ ሠፊ የaperture ክፍተት (ትንሽ የF-stop ቁጥር) ሲኖረው ደግሞ shallow depth of field ወይም ካሜራው አንድ ነገር ብቻ ጥርት አድርጎ እያሳየ ከጀርባ/ከፊት ያለውን ያደበዝዘዋል ማለት ነው።

  1. Depth of field

Depth of fieldተምልካቹ ከፊት, ከመሀል ወይም ከጀርባ ያለው ነገር ላይ አትኩሮቱን እንዲያደርግ የምናደርግበት መንገድ ነው። Depth of field በ Focal length እና በ Aperture መጠን የሚወሰን ነው።በwide depth of field ግዜ ሁሉም ነገር ጥርት ብሎ ሲታይ በshallow depth of field ግዜ ደግሞ ካሜራው አንድ ነገር ብቻ ጥርት አድርጎ እያሳየ ከፊት/ከመሀል/ከጀርባ ያለውን ያደበዝዘዋል ማለት ነው።

  1. Bokeh

አንድ ምስል shallow depth of field ሲኖረው በምስሉ ውስጥ የሚታየው የተወሰነ ክፍል የደበዘዘ ይሆናል፤ ይህ የመደብዘዝ መጠን Bokeh ብለን እንጠራዋለን። Bokeh የምስሉን ውበት ከመጨመሩም በላይ የተመልካቹን አይን ባለሙያው ወደ ፈለገው ቦታ እንዲያርፍ ያደርገዋል።

  1. ISO and Noise

ISO (International Organization for Standardization) በዲጂታል ሲኒማቶግራፊ ግዜ የሴንሰሩን ብርሃን የመቀበል አቅም/መጠን የምንለካበት መንገድ ነው። ISO ሲጨምር የብርሃን መጠን እና Noise አብረው ይጨምራሉ። ለምሳሌ ISO400 ከ_ISO200 ሁለት እጥፍ የብርሃን መጠን እና Noise አለው።

Noise የምንለው በምሰል ላይ የሚታዩ ያልተፈለጉ ጥቃቅን እና የሚርገበገቡ ነጠብጣቦች ሲሆኑ አንስተኛ ISO እና ጥሩ የብርሃን መጠን  በመጠቀም መቀነስ  እንችላለን።

  1. Compression and Bit Rate

Compression: ከካሜራው የመጣውን data (ቪዲዮ እና ድምፅ) ጥራቱን እንደጠበቀ አንስተኛ መጠን ኖሮት እንዲቀመጥ የምናደርግበት መንገድ ሲሆን ይህም ትንሽ መጠን ባላቸው የሚሞሪ ካርዶች ወይም ዳታ ማስቀመጫዎች ላይ በዛት ያለው እና ረጅም ቪዲዮችን እንድናስቀምጥ ይረዳናል።የተለያዩ Compress ማደረጊያ ቀመሮች እና መንገዶች አሉ እነዚህንም Codecs እንላቸዋለን።H264 እና MJPEG በስፋት የምንጠቀምባቸው የcodec አይነቶች ናቸው።RAW የምንለው ዳታዎቹ ምንም compress ያልተደረጉ እና ከሴንሰሩ ቀጥታ እንደመጡ የሚቀመጡ ምስሎችን ነው።

Bitrateአንድ codec በሰከንድ የሚያስተላልፈው/የሚቀዳው የዳታ መጠን ሲሆን የሚገለፀውም በMbps ወይም Mb/s ነው። ። ትልቅ bit rate ያላቸው ትልቅ ቦታን ቢይዙም የተሻለ ጥራት ግን ይኖራቸዋል።

ሰለ አስሩ ሊያውቋቸው የሚገቡ መሰረታዊ የዲጂታል ሲኒማቶግራፊ ሀሳቦችያካፈልኳችሁን እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። በሚቀጠለው ፅሁፌ ደግሞ ስለ አስሩ የፍቅር ጓደኛዬንየማስደስትባቸው መንገዶች ላካፍላችሁ ስለምችል ምንም አመታትን ቢፈጅሌሎች ፅሁፎቼን እያነበባችሁ በተስፋ እንድትጠብቁ እጠይቃለሁ።

ሰለ አስሩ ሊያውቋቸው የሚገቡ መሰረታዊ የዲጂታል ሲኒማቶግራፊ ሀሳቦችየሚሉት ወይም የሚጠይቁት አለ? በሚቀጥለው ፅሁፍስ ስለምን ማወቅ ይፈልጋሉ?ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ይፃፉልኝ።

ሰማኝጌታ አይችሉህም(ኪያ)