Color grading ምንድን ነው?

Color ወይም ቀለም ታሪከን ከምንገልፅበት መሳሪያዎች ዋነኛው ነው። ቀለም ቅርፅን, ስሜትን እና ታሪክን ለተመልካች እንድናስተላልፍ ይረዳናል፤ ይህንንም ለማድረግ ቀለምን መቀየር እና ማስተካከል ይኖርብናል፤ ይህንንም ሂደት color grading እንለዋለን።

Color grading ባለሙያው ፊልሙ እንዲያስተላልፍ የመረጠውን ታሪክ, ስሜት እና ቀለም የተለያዩ ቀለምን ማሰተካከያ እና መቀያየሪያ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ይበልጥ የተሳካ እንዲሆን ይረዳዋል። ነገርግን color grading መጀመሪያውኑ ፊልሙ ውስጥ ያሉትን ቀለሞች ብቻ በመጠቀም ስለሚቀያይር color grade ጥሩ ሊሆን የሚችለው እንደተቀረፀው ሰራ ነው። ሰለዚህም ጥሩ color grade የሚጀምረው ከቀረፃ በኋላ ሳይሆን ቀረፃ ላይ ባሉት አካላት ነው፤ ጥሩ ልብሶች፤ ጥሩ የቀረፃ ቦታዎች፤ ጥሩ የብርሃን ስርጭት ወ.ዘ.ተ.  ለዚህም ምሳሌ ሊሆን የሚችል ሰሞኑን ካየኋቸው ምስሎች ውስጥ በሳቢሳ ፊልም ፕሮዳክሽን ቀርቦ በሰውመሆን ዳይሬክት እየተደረገ በመሰራት ላይ ያለውዓለሜ ፊልም አንዱ ነው። ከታች በምስሉ ላይ ማየት እንደሚቻለው ቀለሞቹ ለአይን የማይረብሹ የተዋኗያን ስሜት የሚገልፁናቸው። የፍሬሙ compostion ቀለሙ ይበልጥ የተሳካ እንዲሆን አድርጎታል።

የcolor grading እና color correction ልዩነት

Color correction እና  Color gradingን አብዛኛውን ግዜ እንደ አንድ አይነት ቃል ብዙዎች ይጠቀሙታል፤ ነገርግን ለሁለቱም አንድ አይነት መሳሪያዎችን ብንጠቀምም በጣም የተለያዩ ስራዎች ናቸው።

Color correction የምንለው እያንዳንዱን የአንድ scene ቀረፃዎች ወደ አንድ ወጥ የሆነ የምስል አይነት ለማምጣት የምንጠቀምበት መንገድን ነው። በተለያዩ ካሜራዎች ወይም ቀናት የቀረፅናቸውን ምስሎች አንድ አይነት ቀለም እንዲኖራቸው ለማደረግ ይረዳናል።

Color grading ደግሞ አንድ ወጥ የሆነ ምስል እንዲኖራቸው color correct ያደረግናቸውን ምስሎች ታሪኩን በሚደግፍ ሁኔታ ወደ ተወሰነ የምስል ቀለም ዘይቤ የምንቀይርበት መንገድ ነው።

Color grading ለምን ይጠቅማል?

አሁን ባለንበት የዲጂታል ፊልም ስራ ግዜ color grading እንደምርጫ ሳይሆን እንደግዴታ እየሆነ የመጣ ጥበብ ነው።Color grading ባለሙያው ፊልሙ እንዲያስተላልፍ የመረጠውን ታሪክ እና ስሜት በተሳካ መልኩ እንዲያቀርብ ይረዳዋል።

The matrixእና The notebook የፊልም ቀለማቸው እንደ ታሪካቸው በጣም የተለያየ ነው። The matrix ሳይንሳዊ ፊልም እንደመሆኑ መጠን ቀለሙም ከምናቀው ተፈጥሯዊ ቀለም የተለየ ወደ አረንጓዴ ያመዘነ ነው። The notebook ግን የፍቅር ታሪክ ሰለሆነ ተመልካቹ እራሱን በተዋናዮቹ ቦታ አድርጎ ስሜታቸው እንዲሰማው ኑሯቸውን እንዲኖር ቀለሞቹ ተፈጥሯዊ እና የተለመዱ ሆነው ቀርበዋል። ስለዚህም color grading በታሪኩ እና በተመልካቹ  ላይ የሚፈጥረውን ስሜት በቀላሉ ማየት ይለብንም።

ለcolor grading የምንጠቀማቸው ሶፍትዌሮች ምንድን ናቸው?

ብዙ ስራዎች ላይ የተለያዩ color grading ሶፍትዌሮችን ተጠቅሜያለሁ። የተጠቀምኳቸው ሶፍትዌሮች እንደሰራው ፍጥነት እና አይነት ይለያያሉ። ቀለል ላሉ ሰራዎች ኤዲቲንግ ሶፍትዌሮች ላይ ያሉትን የcolor grading ኢፌክቶችን ስጠቀም ከበድ ላሉ እና ብዙ ስራ ለሚያስፈልጋቸው ሰራዎች ደግሞ እንደ Aftereffects Color Finesse, Magicbullet looks, Speedgrade  እናDavinci resolve, ለcolor grading ታሰበው የተሰሩትን ሶፍትዌሮች እጠቀማለሁ። ከዚህ በፊትም እንደፃፍኩት የምንጠቀመው ሶፍትዌር ያለእኛ እውቀት እና ስራ ምንም ነገር አይጨምርልንም። ሁሉም ሶፍትዌሮች ተመሳሳይ ቀለምን ማሰተካከያ መሳሪያዎች ሲኖራቸው የሚለያዩት ግን በሚከተሉት ሂደት ነው። የcolor grading ዋናውን ሃሳብ ከተረዳን የትኛውምንም ሶፍትዌር ብንጠቀም ጥሩ ውጤት ማግኘታችን የማይቀር ነው።

Color grading ሁልግዜ ጠንካራ እና የሚታይ መሆን የለበትም። ጥሩ color grade ለእይታ የሚያምር ብቻ ሳይሆን በፊልሙ ታሪክ, ገፀባህሪያት እና ሰሜት የሚመራ መሆን አለበት።በመጨረሻም በሚቀጥለው ፅሁፌ ላይ ለcolor grading ምሳሌ የሚሆን ቪዲዮ ይዤ ስለምቀርብ እስከዛ እቺን ፅሁፍ እንደቡና ቁርስ እያነበባችሁ እንድትጠብቁኝ አሳስባለሁ።

እርሶስ ስለColor grading ምን የሚሉት አለ? በሚቀጥለው ፅሁፍስ ስለምን ማወቅ ይፈልጋሉ? ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ይፃፉልኝ።

ሰማኝጌታ አይችሉህም፤ ኪያ