አሁንም በባለቁጥር ርዕስ ፅሁፍ ተመልሻለሁ። ከጥቂት ወራት በፊት አንድ የማስታወቂያ ስራ ላይ Director of photography, Editor እና vfx artist ሆኜ ሰርቼ ነበር። አብዛኛዎቹ ቀረፃዎች በchroma keying እንዲቀረፁ ያቀረብኩትን ሃሳብ ፕሮዲውሰሩ በመቀበሉ ገንዘቡን ከመቆጠብም በላይ ስራው በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቅ አስችሏል። እናንተም ስራችሁን በአንስተኛ ወጪ እና በፍጥነት እንድታጠናቅቁ ስለ chroma keying ጥቂት ልበላችሁ።
Chroma የሚለው ቃል Color ወይም ቀለም ማለት ነው። Chroma keyingሁለት እና ከዛበላይ የሆኑ ምስሎችን በቀለማቸው አማካኝነት key በማደረግ ወይም በመቁረጥወደ አንድ ምስል የምንቀላቅልበት መንገድ ነው።አብዛኛውን ግዜ ለዚህ ሂደት የምንጠቀማቸው ቀለሞች አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ናቸው። የካሜራ ሴንሰር አረንጓዴ ቀለሞችን ከሌሎች ቀለሞች በብዛት መዝግቦ ሰለሚይዝ፤ አረንጓዴ ቀለም ቻናል ከሌሎች ቻናሎች(ቀይ እና ሰማያዊ) ከnoise የጠራ ይሆናል፤ ይህም ዋነኛው ተመራጭ እንዲሆን ያደርገዋል።
አብዛኛውን ግዜ ይህንን ሂደት የምናየው በአየር ንብረት ትንበያ ፕሮግራሞች ላይ ነው። አቅራቢው አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ቀለም ካለው ጨርቅ ወይም ግድግዳ ፊት ይቆምና አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ቀለሙ በአስፈላጊው የአየር ንብረት መረጃ ይተካል። አቅራቢው የጀርባውን ቀለም አይነት ልብስ ካደረገ ልብሱም ሊቆረጥ ወይም key ሊደረግ ስለሚችል የተለየ አይነት ቀለም ያለው ልብስ ማድረግ ይኖርበታል። ብዙ የvisual effect ቀረፃዎች የሚካሄዱትም ይህንኑ መንገድን በመጠቀም ነው።
አስፈላጊ እና መሰረታዊ የchroma key ሃሳቦች ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን 5 ነጥቦች ከዚህ በታች በዝርዝር ፅፌያቸዋለሁ
- የጀርባ ቀለም (Screen color)
Chroma keying ሲታሰብ የመጀመሪያው ጥያቄ የጀርባው ቀለም ምን መሆን አለበት የሚል ነው። ከላይ እንደተገለፀው አብዛኛውን ግዜ ለዚህ ሂደት የምንጠቀማቸው ቀለሞች አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ናቸው። የካሜራ ሴንሰር አረንጓዴ ቀለሞችን ከሌሎች ቀለሞች በብዛት መዝግቦ ሰለሚይዝ አረንጓዴ ቀለም ቻናል ከሌሎች ቻናሎች(ቀይ እና ሰማያዊ) ከnoise የጠራ ይሆናል፤ ይህም ዋነኛው ተመራጭ እንዲሆን ያደርገዋል። እንደ ጀርባ (screen) የምንጠቀምበት መሳሪያ ጨርቅ, ካርቶን ወይንም በተመረጠው ቀለም የተቀባ ግድግዳ ሊሆን ይችላል። ነገርግን ስክሪኑ ቀለሙን በዙሪያው የማያንፀባርቅ መሆን ይኖርበታል።
- ብርሃን (Lighting)
ለChroma key በምንዘጋጅበት ግዜ ከባዱ እና አሳሳቢው ጉዳይ ስክሪኑን ከጥላ የፀዳ እና የተደላደለ የብርሃን ስርጭት እንዲኖረው ማድረግ ነው። ይህንን ለማድረግም መጀመሪያ ብርሃኑን ለስክሪኑ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከል ይኖርብናል ከዛም በመቀጠል የሚቀረፀውን ሰው ብርሃን መጠን ወደ ማስተካከል መሄድ እንችላለን። `
- ቦታ (Space)
የሚቀረፀው ሰው በተቻለው መጠን ያህል ከስክሪኑ መራቅ ይኖርበታል፤ ይህም ጥላው በስክሪኑ ላይ እንዳያርፍ ከመርዳቱም በላይ በስክሪኑ ምክንያት የሚንፀባረቅበትን ቀለም መቀነስ እንዲቻል ያደርጋል። ስለዚህም የምንሰራበትን ቦታ ክፍተት ስራ ከመጀመራችን በፊት ማሰብ እና ማስተካከል ይኖርብናል።
- ካሜራ (Camera)
የካሜራችን ከለር የመመዝገብን ችሎታ Chroma subsamplingእንለዋለን። Chroma subsampling ወደ ካሜራችን ከገባው ብርሃን ውስጥ የካሜራው ሴንሰር ምን ያህል ከለሮችን በሙሉ ወይንም ናሙና(sample) በመውሰድ መዝግቧል የሚለውን የሚገልፅልን ቃል ነው። አብዛኛዎቹ DSLR ካሜራዎች 4:2:0 chroma subsamplingን ይጠቀማሉ። 4:2:2 እና 4:4:4 chorma subsamplingን የሚጠቀሙ ካሜራውችን መጠቀም ወደ ሴንሰሩ የሚገባውን የከለር መረጃ መጠንን ስለሚጨምርልን የተሻለ chroma key ልናገኝ እንችላለን።
- ሶፍትዌር (Software)
አብዛኛዎቹ Non-Linear editing softwares ወይም ቀጥተኛ ያልሆኑ ኤዲቲንግ ሶፍትዌሮች key የሚያደርግ በውስጣቸው የተጫነ ኢፌክት አላቸው። እኔ የምጠቀመው እና እስካሁን ካየኋቸው ፕሮፌሽናል key ማደረጊያ ሶፍትዌሮች የወደድኩት ግን “Keylight” የተሰኘውን Adobe After effects እና Nuke ውስጥ ያለውን ሶፍትዌር ነው።
ሰለchroma keying መታወቅ አለባቸው ብዬ ያሰብኳቸው ነጥቦች እነዚህ ነበሩ።keylightን በመጠቀም እንዴት key ማደረግ ወይም መቁረጥ እንደሚቻል ማወቅ የሚፈልግ ሰው ካለ በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ላይ ይፃፍልኝ እና በቪዲዮ የታገዘ ምሳሌ በሚቀጥለው ፅሁፌ ላይ አቀርባለሁ። chroma key በጣም ታላላቅ የሆኑ ፊልሞች ውስጥ እጅግ በጣም ትልቅ ሚናን የተጫወተ አስፈላጊ መንገድ ነው። ይህንንም ስራ እናንተም በየሰራችሁ ላይ እንደምትሞክሩት ተስፋ አደርጋለሁ።
እርሶስ ስለChroma keying ምን የሚሉት አለ?በሚቀጥለው ፅሁፍስ ስለምን ማወቅ ይፈልጋሉ?ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ይፃፉልኝ።
ሰማኝጌታ አይችሉህም፤ ኪያ
Leave A Comment