ሰሞኑን የመመረቂያ ፅሁፌን ፕሮፖዛል ስራ ላይ ስለነበርኩ መጦመር አልቻልኩም ነበር። ከዚህ በፊት የነበረው ፅሁፌን ከ24 ቀናት በፊት ነበር የፃፍኩት። 24 የሚለው ቁጥር ሳላቀው በጭንቅላቴ  ተቀርፆ ሁልግዜ frame rate ትዝ ይለኛል። ሰለዚህም በዚህኛው ፅሁፌ ሰለframe rate ላወራችሁ ተገደድኩ።

የፊልም ሰራ ብዙ ነገሮችን ማወቅ ይጠይቃል። ከዚህም ውስጥ frame rate ዋነኛው እና መሰረታዊ የምንለው ነው። Frame rate በፊልማችን ገፅታ ስሜት እና ምስል ላይ በሚገርም መልኩ ተፅኖ ያሳድራል።

በአንድ ሰከንድ ውስጥ የሚታዩትን የምስል ተረታ ብዛት በframe rate እንገልፀዋለን። እነዚህ የሚታዩትን ነጠላ ምስሎች ደግሞ Frame እንላቸዋለን። Frame rate የሚለካውም በFPS (frames per second) ነው። አንድ ቪዲዮ 24FPS ነው ስንል, በቪዲዮው ውስጥ ያለ የአንድ ሰከንድ እይታ 24 ተከታታይ ምስሎችን ይዟል ማለት ነው። ከነዚህም ምስሎች ውስጥ አንዱን ነጠላ ምስል frame ብለን እንጠራዋለን።

የተለያዩ የframe rate መጠኖች አሉ፤ እነዚህም 24p, 25p, 30p, 48p, 50/60i, 50/60p ወ.ዘ.ተ. ናቸው። ከ1927-1930ዎቹ (እ.ኤ.አ) ግዜ ጀምሮ 24fps እንደ ቋሚ የፊልም frame rate ሆኖ ተወስዷል። ‘p’ እና ‘i’ ፊደሎች progressive እና interlaced scanning የሚለውን ለመለየት የምንጠቀምባቸው ናቸው። ሰለprogressive እና  interlaced scanning በዚህኛው ፅሁፊ ላይ አስረድቻለሁ።

በዚህ ፅሁፍ ላይ በጣም ለማሳሰብ የምፈልገው ነጥብ የframe rate መጠን በአንድ ቪዲዮ ላይ ያለን የእንቅስቃሴ እይታን እንዴት ሊቀይር እንደሚችል ነው። ትልልቅ frame rate መጠቀም በአንድ ሰከንድ ውስጥ ብዙ ምስሎች እንዲኖሩን ስለሚረዳ ለዘገምተኛ እንቅስቃሴ ወይም ለslow motion በጣም ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ በ60fps የተቀረፀ የአንድ ሰከንድ ቪዲዮ ወድ 24fps ስንቀይረው 2.5 ሰከንድ ርዝመት ይኖረዋል። አንስተኛ frame rate መጠቀም ደግሞ በተቃራኒው ቀጥ ቀጥ ያለ  እንደ ቻርሊ ቻፕሊን አይነት ፊልም የሚመስል ምስል ይሰጠናል።

በአንድ ፊልም ላይ የማይለዋወጥ frame rate መጠቀም ለአይን የማይረብሽ ምስል እና ፕሮፌሽናል ምስል እንድናገኝ ይረዳናል።frame rate በአንድ ፊልም እይታ ላይ የሚያሳየውን ለውጥ ለመመልከት ሁለት የፊልም አይነቶችን እንመልከት። የላቲን ተከታታይ ድራማዎች እና የአሜሪካ ተከታታይ ድራማዎች ያላቸው የምስል ለውጥ በጣም ግልፅ የሆነ ነው። የሚያወሩትን ነገር ሳይሰሙ የየትኛው ሀገር ፊልም እንደሆነ መለየት ቀላል ነው። ይህም ከሆነበት ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው የላቲን እና የአሜሪካ ፊልም ያላቸው የframe rate ልዩነት ነው።

ከዚህ በኋላ በምትሰሩት ስራ ላይ frame rateን ካሜራውን ስታበሩት እንዳገኛችሁት እንደማትወስዱ ተስፋ አደርጋለሁ።

እርሶስ ስለFrame Rate ምን የሚሉት አለ? በሚቀጥለው ፅሁፍስ ስለምን ማወቅ ይፈልጋሉ? ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ይፃፉልኝ።

ሰማኝጌታ አይችሉህም፤ ኪያ